ስለ ካናዳ

ካናዳ በተደጋጋሚ የአለማችን ቁጥር አንድ ምርጥ አገር የሚል ክብር የተጎናጸፈች አገር ናት፡፡ ካናዳ በአሁኑ ወቅትም በኑሮ ደረጃ ጥራት ከአለማችን አገራት በ1ኛ ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው፡፡ በካናዳ ትምህርትዎን ይከታተሉ፤ በመላው አለም ስመጥር በሆኑ ዝነኛ መምህራንና የአካዳሚው መስክ ከዋክብት የሚሰጠውን በአለማቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸረው ደረጃውን የጠበቀ ምርጥ ትምህርት ያገኛሉ፡፡

አንዳንድ እውነታዎች
-36.3 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርባታል
-250 ብሔር ብሔረሰቦች ይገኙባታል
-6.4 ሚሊዮን ሰዎች የስደተኞች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ናቸው
-60+ የአቦርጅኖች ቋንቋዎች ይነገሩባታል
-10 አውራጃዎችና 3 ግዛቶች አሏት
-ኪሎ ሜትር የሚረዝም የባህር ዳርቻ አላት - በአለማችን ረጅሙ ነው
-በ3 ውቅያኖሶች ዙሪያዋን ተከብባለች 

ለምን ካናዳ?

ለአለማቀፍ ተማሪዎች የዋጋ ቅናሾች

እንደ አለማቀፍ ተማሪ ካናዳ ውስጥ የጉዞ የዋጋ ቅናሽ ይደረግልዎታል፡፡ ሬስቶራንቶች፣ ሆቴሎች፣ አየር መንገዶች፣ ባቡሮችና ሌሎች የጉዞ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለተማሪዎች ልዩ የዋጋ ቅናሽ ያደርጋሉ፡፡ የዋጋ ቅናሾች ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ የተማሪ መታወቂያ ካርድ መያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡

ከተመረቁ በኋላ በካናዳ የስራ ልምድ ያግኙ

የካናዳ መንግስት በአገሪቱ ከሚገኝ የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ ላገኙ ወይም በዲግሪ ፕሮግራም ተመርቀው የስራ ልምድ ማግኘት ለሚፈልጉ ተማሪዎች ልዩ የስራ ፕሮግራም ዕድል ይሰጣል፡፡
ይህ አሰራር የሙያ አድማስን እያሰፉና ሙያዊ ክህሎትን የበለጠ እያዳበሩ ኑሮን በካናዳ ለመቀጠል እጅግ ሁነኛ አማራጭ ነው፡

አለማቀፍ ደረጃውን ከጠበቀ ትምህርት ተጠቃሚ ይሁኑ

የካናዳ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጧቸው ዲፕሎማዎች በመላው አለም እውቅናን ያገኙ ናቸው፡፡ ታይምስ ሃየር ኢዱኬሽን የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው የአለማችን ምርጥ 100 ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ አምስት የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች ተካትተውበታል፡፡

የቋንቋ ብዝሃነት ባለበት አካባቢ ይኑሩ

ካናዳ ሁለት ቋንቋዎች የሚነገሩባት አገር ስትሆን፣ በካናዳ መማር የቋንቋ ክህሎትዎን ለማሳደግና የተሻለ ሙያ ባለቤት የመሆን ዕድልዎን የሚያሰፋና የመጻይ ጊዜ ተስፋዎን የሚያመልም መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ በፈረንሳይና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰጡት ፈተናዎችና የቤት ስራዎች፣ በካናዳ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ቁልፍ ስፍራ የሚሰጣቸው ባህልና ማህበረሰብን የሚያበለጽጉ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው

በዚያው የመቅረት ዕድል

በካናዳ ትምህርትዎን ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ፣ ቀጣይ ህይወትዎን በዚያው ለማድረግና ቀሪ ዘመንዎን በካናዳ ለመግፋት ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ በዲግሪ የተመረቁና የአንድ አመት የስራ ልምድ ያላቸው አመልካቾች፣ የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው፤ ወደካናዳ ያደረጉትን ጊዚያዊ ጉዞ ወደቋሚና ዘላቂ የህይወት ዘመን ቆይታ መቀየር የሚችሉት፡፡

እየተማሩ ይስሩ

አለማቀፍ ተማሪዎች በትምህርት ላይ እያሉ በሳምንት እስከ 20 ሰዓታት፣ በእረፍት ጊዚያቸው ደግሞ እስከ 40 ሰዓታት የትርፍ ሰዓት ስራ መስራት ይችላሉ፡፡ በሰዓት በአማካይ ከ8 እስከ 10 የካናዳ ዶላር ገቢ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ተማሪዎች ከካምፓስ ውጭ በጋራ የሚከናወኑ የሙሉ ጊዜ ስራዎችን መስራት የሚችሉ ሲሆን፣ በዚህም በሰዓት በአማካይ ከ10 እስከ 15 የካናዳ ዶላር ወይም በወር ከ400 እስከ 1000 የካናዳ ዶላር ገቢ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የተማሪነት ህይወት

የካናዳ የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቅጽር ግቢዎች ዘመኑ ባፈራቸው ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች የታጠሩ ብቻ አይደሉም፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሌሎች እጅግ ዘመናዊና ደስታን የሚያጎናጽፉ አገልግሎቶችንም ለተማሪዎች ያቀርባሉ፡፡ የካናዳ የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቅጽር ግቢዎች፣ በኦሎምፒክ የጥራት ደረጃ ከተሰሩ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እስከ ግዙፍ የኮንሰርት አዳራሾችና የኪነጥበብ ጋለሪዎች እጅግ ሰፊ የመማሪያና የመዝናኛ ዕድሎችን ለተማሪዎቻቸው እነሆ ይላሉ፡፡
አለማቀፍ ተማሪዎች በትምህርት ወቅቶች በሳምንት ለ20 ሰዓታት፣ በእረፍት ጊዚያት ደግሞ የሙሉ ጊዜ ስራ መስራት ይችላሉ፡፡
በትምህርት ፈቃድ ሰነድዎ ውስጥ እንደተጠቀሰው፣ የስራ ፈቃድ ባያገኙም በግቢ ውስጥ ወይም ከግቢ ውጭ ስራዎችን መስራት ይችላሉ፡፡
ከግቢ ውጭ መስራት የሚችሉት እውቅና ባለው የትምህርት ተቋም ተመዝግበው ትምህርት ከጀመሩ፣ የትምህርት ፕሮግራምዎ ወደ ዲግሪ የሚያመሩ ከሆኑና የማህበራዊ ኢንሹራንስ ቁጥር እንዲሰጥዎት ካመለከቱ ብቻ ነው፡፡
በትምህርት ወቅት በሳምንት ከ20 ሰዓታት በላይ ስራ መስራት፣ የትምህርት ፈቃድዎ ላይ የተዘረዘሩትን ደንብና ግዴታዎች መጣስ ነው፡፡ ይህን ድርጊት ከፈጸሙ፣ የተማሪነት እውቅናዎን ሊነጠቁና በቀጣይም የትምህርትና የስራ ፈቃድ ቢያቀርቡ ተቀባይነት ላያገኙ፣ አልፎ ተርፎም አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ሊወሰንብዎት ይችላል፡፡

ብዙ ይትምህርት ምርጫዎች

ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች

ለመጀመሪያ ዲግሪ

የታደሰ ፓስፖርት

የሃሳብ መግለጫ ጽሁፍ (ካስፈለገ)

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ማረጋገጫ (IELTS or TOEFL)

የትምህርት ማስረጃዎችና ሰርተፊኬቶች

ለሁለተኛ ዲግሪ

የታደሰ ፓስፖርት

የሃሳብ መግለጫ ጽሁፍ (ካስፈለገ)

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ማረጋገጫ (IELTS or TOEFL)

የትምህርት ማስረጃዎችና ሰርተፊኬቶች

ይከተሉን!

አድራሻ

1. ቦሌ ከ መድሃኔአለም ሞል ፊት ለፊት፣ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ

+251 115 58 97 94 , +251 116 67 13 76 , +251 116 67 16 93 , +251 942 12 96 11

አድራሻ

2. ለቡ ከጋራ ማርት ፊት ለፊት፣ ፎዚያና ህንጻ 5ኛ ፎቅ

+251 11 470 10 00 , +251 114 70 04 36 , +251 114 70 04 37 , hello@lineaddis.com