የተመቸ የኑኖ ደረጃ
ፓስፖርት
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትራንስክሪፕት (9-12)
የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት
ፓስፖርት
የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት/ የተማሪ ኮፒ
ዲግሪ ሰርተፊኬት/ ቴምፖ
➖በምታመለክቱበት ጊዜ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁ ወይም የ12ኛ ክፍል ተማሪ መሆን አለባችሁ
➖የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆናችሁ ከትምህርት ቤታችሁ ደብዳቤ ማጻፍ ይኖርባችኋል
➖መጨረሻ ትምህርትዎን ያጠናቀቁበት ጊዜ ከ5 አመት መብለጥ የለበትም፡፡
➖የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ ወይም ትምህርት ቤት የሚመረቁበትን ቀን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
➖ለሁለተኛ ዲግሪ የሚያመለክቱ አመልካቾች ኮስት ሼሪንግና ሌሎች የሚከፈሉ ወጪዎችን ከፍለው ዋናው ሰነዳቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
➖የአመልካቾች አላማ መሆን ያለበት መማር ብቻ ነው፡፡ ለሌላ አላማዎች ወይም ቪዛ ብቻ ለማግኘት የሚመጡ አመልካቾችን አንቀበልም፡፡
ከተርኪሽ ሪፐብሊክ ቆንስላ የተማሪ ቪዛ ማግኘት ግድ ይለዎታል፡፡ ቪዛው ለ90 ቀናት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ የመኖሪያ ፈቃድ እስከሚያገኙበት ጊዜ ድረስ ከቱርክ መውጣትም ወደ ቱርክ ተመልሶ መግባትም አይፈቀድልዎትም፡፡
የዩኒቨርሲቲ ምዝገባዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ማድረግ የሚገባዎት እጅግ አስፈላጊ ነገር፣ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ማስገባት ነው፡፡
ቱርክ ውስጥ እስካሉ ድረስ በመኖሪያ ካርድዎ እና ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ በሚሰጥዎት የውጭ መታወቂያ ቁጥር (YU) አማካይነት ማንኛውንም መደበኛ ግብይት መፈጸም ይችላሉ፡፡ የመኖሪያ ካርድዎ የአገልግሎት መስጫ ጊዜው እስካላበቃ ድረስ ከቱርክ ለመውጣትና ለመግባት ሊያገለግልዎት ስለሚችል አዲስ ቪዛ ማግኘት ግድ አይልዎትም፡፡ የመኖሪያ ፈቃድዎ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜው ከመድረሱ በፊት ማሳደስ እንዳለብዎት አይርሱ፡፡
• ፓስፖርት/ ቢያንስ ለ90 ቀናት አገልግሎት መስጠት የሚችል
• የተፈረመበት የቱርክ የተማሪ ቪዛ ማመልከቻ ቅጽ
• 2 ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶ ግራፎች
• ከዩኒቨርሲቲዎ የተቀባይነት ደብዳቤ
• በቱርክ ለሚቆዩበት ጊዜ በሙሉ የጉዞ ኢንሹራንስ ሽፋን
• ወደ ቱርክ የሚደረግ የአውሮፕላን በረራ ትኬት
• በቱርክ ቆይታዎ ለትምህርትና ለኑሮ ወጪዎትን ለማገዝ የሚችል በቂ የገንዘብ ሃብት እንዳለዎት ማረጋገጫ
• የቪዛ ፕሮሰስ ክፍያ
• በቱርክ ማረፊያ ቤት እንዳለዎት ማረጋገ
• ቀደምት የትምህርት ማስረጃዎች ወይም ዲፕሎማዎች
1. የሚፈልጉትን ዩኒቨርሲቲና መማር የሚፈልጉትን ትምህርት ከድረ-ገጻችን፣ ከቴሌግራም ቦት ወይም ድርጅታችን ድረስ በአካል በመምጣት ይምረጡ፡፡
2. የማመልከቻ ሰነዶቻችሁን ስካን በማድረግ ከሚከተሉት አማራጮች በአንዱ ገቢ ያድርጉ፡-
Email: hello@lineaddis.com
Telegram : @lineaddis2
በአካል ወደ ድርጅታችን በመምጣት
3. ወደ ድርጅታችን በመምጣት ቅድመ ክፍያ እና የማመልከቻ ክፍያ ይክፈሉ፤ የስምምነት ውል ይፈጽሙ፡፡ የሚኖሩት ከአዲስ አበባ ራቅ ባለ አካባቢ ከሆነ፣ ስምምነቱን በድረገጽ አማካይነት በኢንተርኔት መፈጸም እንችላለን፡፡
4. ከዩኒቨርሲቲው ጊዚያዊ የጥያቄ ደብዳቤ እስኪመጣ ይጠብቁ
5. የትምህርት ክፍያ እና የቪዛ ማስፈጸሚያ ክፍያ በዩኒቨርሲቲው የባንክ ሒሳብ ይፈጽሙ፡፡
6. የቪዛ ማመልከቻ ሰነዶችን አዘጋጅተው ይላኩ፡፡
7. ከዩኒቨርሲቲው የተማሪ መግቢያ ፈቃድ ያግኙ፤ ከዚያም ወደ ቱርክ ይጓዙ፡፡
በቱርክ ለትህምርት በሚኖርዎት ቆይታ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትዎን ለማሟላት የተለያዩ አማራጮች አሉዎት፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ቅጽር ግቢ ውስጥ በሚገኙ ዶርሞች፣ የቱርክ ከፍተኛ ትምህርት ብድርና ሆስቴሎች ኢንስቲቲዩሽን በሚያስተዳድራቸው የመንግስት ዶርሞች፣ በግል ዶርሞች ወይም በከተሞች በሚገኙ የኪራይ አፓርታማዎች ውስጥ መኖር ይችላሉ፡፡
በቱርክ ሁሉም የመንግስትና የዩኒቨርሲቲ ዶርሞች ለሴትና ለወንድ ተማሪዎች ተለይተው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በመኝታ ክፍሎችና በጋራ መገልገያ ስፍራዎች ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ የቤት ዕቃዎች በሙሉ ተሟልተው ይገኛሉ፡፡ ዶርሞች ለሁሉም ተማሪዎች የባለገመድና ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት የተሟላላቸው ናቸው፡፡ አንዳንድ ዶርሞች የራሳቸው የተለየ ካፊቴሪያ ያላቸው ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ ቁርስና ራት ያቀርባሉ፡፡ የቱርክ ከፍተኛ ትምህርት ብድርና ሆስቴሎች ኢንስቲቲዩሽን የሚያስተዳድራቸው ዶርሞች በወር እስከ 40 የአሜሪካ ዶላር ያስከፍላሉ፡፡
ለአለማቀፍ ተማሪዎች ሌላኛው የመኖሪያ ቤት አማራጭ የኪራይ ቤት ነው፡፡ በተለይ በዩኒቨርሲቲዎች አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ተማሪዎች ከጓደኞቻቸው ጋር ቤት እየተከራዩ ይኖራሉ፡፡ 90 ስኩየር ሜትር ስፋት ያለው አንድ ቤት ለመከራየት፣ በወር በአማካይ ከ80 እስከ 280 የአሜሪካ ዶላር ወጪ ይጠይቃል፡፡
ኢስታንቡል ውስጥ የአንድ ሰው ወርሃዊ የኑሮ ወጪ ኪራይን ሳይጨምር እስከ 428 የአሜሪካ ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል፡፡ የሚማሩት ከመዲናዋ ውጭ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ከሆነ፣ ጥሩ ኑሮ ለመኖር በወር እስከ 399 ዶላር ወጪ ሊያስፈልግዎት ይችላል፡፡