የአገሪቱ ስም: የማሌዢያ ፌዴሬሽን
ዋና ከተማ: ኳላላምፑር
የህዝብ ብዛት፡ 31 ሚሊዮን (ተመድ፣ 2012)
የቆዳ ስፋት፡ 329,847 ስኩየር ኪሎሜትር
ዋናዋና ቋንቋዎች፡ ማላይ (ብሔራዊ ቋንቋ)፣ እንግሊዝኛ፣ የቻይንኛ ዘዬዎች፣ ታሚል፣ ቴሌጉ፣ ማላያላም
ዋና ዋና ሃይማኖቶች፡ እስልምና፣ ቡድሂዝም፣ ታኦይዝም፣ ሂንዱዝም፣ ክርስትና፣ ሲኪዝም
አማካይ ዕድሜ፡ 73 አመት (ለወንዶች)፣ 78 አመት (ለሴቶች)
የመገበያያ ገንዘብ፡ ሪንጊት (1 የአሜሪካ ዶላር 4.2 የማሌዢያ ሪንጊት ይመነዘራል)
ፓስፖርት
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትራንስክሪፕት (9-12)
የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት
ፓስፖርት
የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት/ የተማሪ ኮፒ
ዲግሪ ሰርተፊኬት/ ቴምፖ
በማሌዢያ በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ አለማቀፍ ተማሪዎች በሙሉ፣ በሴሚስተር እረፍት ወይም ከ7 ቀናት በላይ በሚቆዩ በዓላት ወቅት በሳምንት ቢበዛ ለ20 ሰዓታት ያህል የትርፍ ሰዓት ስራ መስራት ይፈቀድላቸዋል፡፡
ተማሪዎች ህጋዊ የተማሪነት ይለፍ ወረቀት እስከያዙ ድረስ በሬስቶራንቶች፣ በነዳጅ ማከፋፈያዎች፣ በሚኒ ማርኬቶችና በሆቴሎች መስራት ይችላሉ፡፡ ያም ሆኖ ግን፣ ቀደም ብለው ከኢሚግሬሽን ቢሮ ፈቃድ ማግኘት ግድ ይላቸዋል፡፡
አለማቀፍ ተማሪዎች በገንዘብ ተቀባይነት መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ አለማቀፍ ተማሪዎች በሆቴሎች ዘርፍም በድምጻውያንነት፣ በሙዚቀኛነት ወይም በእንግዶች ግንኙነት መኮንንነት የስራ መስኮች ላይ መሰማራትም አይፈቀድላቸውም፡፡
አለማቀፍ ተማሪዎች ከሞራልና ስነምግባር ውጭ በሆኑ ማንኛውም አይነት ስራዎች ወይም ድርጊቶች ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡
አለማቀፍ ተማሪዎች የትርፍ ሰዓት ስራ ለመስራት መጀመሪያ ማመልከቻ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን፣ ማመልከቻውንም የሚያስገቡት ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት የትምህርት ተቋም በኩል ነው፡፡ አለማቀፍ ተማሪው ከሚማርበት ትምህርት ተቋም ተወካይ ጋር በመሆን በአካል በማሌዢያ ኢሚግሬሽን ቢሮ በመገኘት የትርፍ ሰዓት ስራ ፈቃድ ማመልከቻውን ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
1. የቅርብ ቤተሰቦች የይለፍ ፈቃድ
የማስተርስ እና የፒኤችዲ ተማሪዎች፣ በእነሱ ላይ ጥገኛ የሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን የትምህርት ጊዜያቸው እስኪያበቃ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ማሌዢያ ማምጣት ይፈቀድላቸዋል፡፡ (የቅርብ ቤተሰቦች በሚለው ዝርዝር ውጥ የሚካተቱት የትዳር አጋር፣ ልጆች፣ እናት እና አባት ብቻ ናቸው)
2. መልቲፕል ኢንትሪ ቪዛ/ መመላለስ የሚያስችል ቪዛ
የተማሪ የይለፍ ፈቃድ ወረቀት ያገኙ ተማሪዎችና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው የትምህርት ጊዜው እስከሚጠናቀቅ በሚኖረው ጊዜ ከማሌዢያ ወደመጡበት አገር በተደጋጋሚ መመላለስና መውታት መግባት የሚችሉበት መልቲፕል ኢንትሪ ቪዛ ይሰጣቸዋል፡፡
3. ለተማሪዎች ማሌዢያ ሲደርሱ የሚሰጥ ቪዛ
ወደማሌዢያ ለመግባት ቪዛ መያዝ ግድ ከሆነባቸው አገራት የሚመጡ ወይም በአገራቸው የማሌዢያ ቆንስላ ተወካይ ቢሮ የሌላቸው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት ተማሪዎች፣ ከማሌዢያ የኢሚግሬሽን ቢሮ VAL እስከተሰጣቸው ድረስ ወደ አገሪቱ መግባት ይፈቀድላቸዋል፡፡ ተማሪዎች ልክ ወደ ማሊዢያ ሲገቡ ቪዛ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
4. ማሌዢያ እንደገቡ የሚደረግ የህክምና ምርመራ
ማሌዢያ ከደረሱ በኋላ በሚኖሩት ሰባት ቀናት ውስጥ፣ የህክምና ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብዎታል፡፡ የተቀበለዎት የትምህርት ተቋም ፓስፖርትዎን በመውሰድ የተማሪ የይለፍ ፈቃድ/ ስቲከር የማዘጋጀት ስራውን ያስፈጽምልዎታል፡፡
5. የተማሪ የይለፍ ፈቃድ/ ቪዛ ህጋዊነት
የተማሪ የይለፍ ፈቃድ የሚሰጠው በየአመቱ ነው፡፡ ማመልከቻ በምታስገቡበት ወቅት፣ የፓስፖርታችሁ የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ ጊዜ ከ12 ወራት በላይ የቀረው ቢሆን ይመከራል፡፡