Study in Dubai, UAE

በማሌዢያ ያሉት የኮርስ ምርጫዎች እና ክፍያዎቻቸው

ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች

ለመጀመሪያ ዲግሪ

ፓስፖርት

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትራንስክሪፕት (9-12)

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት

ለሁለተኛ ዲግሪ

ፓስፖርት

የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት/ የተማሪ ኮፒ

ዲግሪ ሰርተፊኬት/ ቴምፖ

መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች

➖በምታመለክቱበት ጊዜ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁ ወይም የ12ኛ ክፍል ተማሪ መሆን አለባችሁ

➖የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆናችሁ ከትምህርት ቤታችሁ ደብዳቤ ማጻፍ ይኖርባችኋል

➖ከHIV እና ከ T.B. ነጻ መሆን አለባችሁ

➖የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ ወይም ትምህርት ቤት የሚመረቁበትን ቀን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

➖ለተማራችሁበት የትምህርት ተቋም የትምህርት ክፍያ ወይም cost sharing መክፈል አለባችሁ

➖ከHIV እና ከ T.B. ነጻ መሆን አለባችሁ

ጠቅላላ መረጃ

የተማሪ መግቢያ ፈቃድ በአብዛኛው በ2 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ የሚሰጥ ሲሆን፣ የሚያገለግለው ደግሞ ለ60 ቀናት ነው፡፡
በመግቢያ ፈቃዱ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ መጓዝ ይችላሉ፡፡የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (ዱባይ) በገቡ በ48 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ፣ የመግቢያ ፈቃድዎና ፓስፖርትዎን መጀመሪያ ለዩኒቨርሲቲው ከዚያ ደግሞ ለኢሚግሬሽን ቢሮ ማስረከብ ግድ ይልዎታል፡፡
በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የተማሪ መኖሪያ ፈቃድ ከማግኘትዎ በፊት የህክምና እና የአሻራ ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብዎታል፡፡
(ለኤችአይቪ/ኤድስ፣ ለጉበት በሽታ ቢ፣ ለጉበት በሽታ ሲ፣ ለቲቢ እና ለስጋደዌ የደም ምርመራና የደረት ኤክስሬይ ምርመራ ያደርጋሉ፡፡ በምርመራዎቹ በሽታዎቹ እንዳሉብዎት ከተረጋገጠ፣ ወደመጡበት አገር እንዲመለሱ ይደረጋሉ፡፡ ይህም በመሆኑ፤ ጉዞ ከማድረግዎ በፊት በአገር ቤት ሳሉ ቀደም ብለው የጤና ምርምራ ማድረግ ይመከራል) በአጠቃላይ እስከ 60 ቀናት የሚፈጀው የተማሪ ቪዛ ፈቃድ ሂደት እንደተጠናቀቀ፣ ፓስፖርትዎ ከኢሚግሬሽን ቢሮ ከተማሪ መኖሪያ ቪዛዎት ጋር ይመለስልዎታል፡፡ ይህን ተከትሎም፣ በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የሚኖር ማንኛውም ሰው የግድ ሊኖረው የሚገባውን የኤሜሬትስ የመታወቂያ ካርድዎን ይቀበላሉ፡፡
የተማሪ መኖሪያ ቪዛዎት የሚያገለግለው ለ12 ወራት ሲሆን፣ በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ጊዜ የትምህርት ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች በየአመቱ ይታደስላቸዋል፡፡ የተማሪ መኖሪያ ቪዛ እና የኤሜሬትስ የመታወቂያ ካርድ ማመልከቻ 1000 የአሜሪካ ዶላር ያህል የሚያስከፍል ሲሆን፣ ክፍያው ለዩኒቨርሲቲዎት የሚፈጸመው የተቀባይነት ደብዳቤ ማግኘትዎን ተከትሎ፣ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች (ወደ ዱባይ) ከመጓዝዎት በፊት ነው፡፡

1. የሚፈልጉትን ዩኒቨርሲቲና መማር የሚፈልጉትን ትምህርት ከድረ-ገጻችን፣ ከቴሌግራም ቦት ወይም ድርጅታችን ድረስ በአካል በመምጣት ይምረጡ፡፡

2. የማመልከቻ ሰነዶቻችሁን ስካን በማድረግ ከሚከተሉት አማራጮች በአንዱ ገቢ ያድርጉ፡-
Email: hello@lineaddis.com
Telegram : @lineaddis2
በአካል ወደ ድርጅታችን በመምጣት

3. ወደ ድርጅታችን በመምጣት ቅድመ ክፍያ እና የማመልከቻ ክፍያ ይክፈሉ፤ የስምምነት ውል ይፈጽሙ፡፡ የሚኖሩት ከአዲስ አበባ ራቅ ባለ አካባቢ ከሆነ፣ ስምምነቱን በድረገጽ አማካይነት በኢንተርኔት መፈጸም እንችላለን፡፡

4. ከዩኒቨርሲቲው ጊዚያዊ የጥያቄ ደብዳቤ እስኪመጣ ይጠብቁ

5. የትምህርት ክፍያ እና የቪዛ ማስፈጸሚያ ክፍያ በዩኒቨርሲቲው የባንክ ሒሳብ ይፈጽሙ፡፡

6. የቪዛ ማመልከቻ ሰነዶችን አዘጋጅተው ይላኩ፡፡

7. ከዩኒቨርሲቲው የተማሪ መግቢያ ፈቃድ ያግኙ፤ ከዚያም ወደ ዱባይ ይጓዙ፡፡

8. የተማሪ ነዋሪነት ቪዛ ማመልከቻ ያቅርቡና ትምህርትዎን ይጀምሩ፡፡

ዱባይ የቅንጦትና የመዝናኛ ከተማ እንደመሆኗ፣ ለኑሮ ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ለትምህርት አላማ ወደ ዱባይ ለመጓዝ እንዳቀደ አንድ አለማቀፍ ተማሪ፣ ለመኖሪያ ቤትና ለሌሎች ወጪዎች ከፍ ያለ ትኩረት መስጠትና በቂ ዝግጅት ማድረግ ይገባዎታል፡፡

መሰረታዊ ነገሮች የተሟሉላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን በወር ከ300 ዶላር ጀምሮ መከራየት ይችላሉ፡፡ በጋራ ለመኖር እስከ 200 ዶላር እንዲሁም፣ የኪራይ አፓርታማዎችን ደግሞ ከ700 ዶላር ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ምግብ፣ መዝናኛ፣ ትራንስፖርትና መጽሐፍትን ጨምሮ በየወሩ ለኑሮ እስከ 900 የአሜሪካ ዶላር ሊያስፈልግዎት ይችላል

ይከተሉን!

አድራሻ

1. ቦሌ ከ መድሃኔአለም ሞል ፊት ለፊት፣ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ

+251 115 58 97 94 , +251 116 67 13 76 , +251 116 67 16 93 , +251 942 12 96 11

አድራሻ

2. ለቡ ከጋራ ማርት ፊት ለፊት፣ ፎዚያና ህንጻ 5ኛ ፎቅ

+251 11 470 10 00 , +251 114 70 04 36 , +251 114 70 04 37 , hello@lineaddis.com