ለምን ሩሲያን ይመርጣሉ

ነጻ የትምህርት እድል

ጥራት ያለው ትምህርት

ባለሁለት ዲግሪ

አለማቀፍ ማህበረሰብ

አስደሳች ይተማሪ ህይወት

ምቹ መኖሪያ

የመቀጠር እድል

አነስተኛ የትምህርት ወጪ

እየተማሩ መስራት

ፕሮግራሞችን ይፈልጉ

ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች

ለመጀመሪያ ዲግሪ

ፓስፖርት

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትራንስክሪፕት (9-12)

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት

ለሁለተኛ ዲግሪ

ፓስፖርት

የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት/ የተማሪ ኮፒ

ዲግሪ ሰርተፊኬት/ ቴምፖ

መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች

➖በምታመለክቱበት ጊዜ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁ ወይም የ12ኛ ክፍል ተማሪ መሆን አለባችሁ

➖የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆናችሁ ከትምህርት ቤታችሁ ደብዳቤ ማጻፍ ይኖርባችኋል

➖መጨረሻ ትምህርትዎን ያጠናቀቁበት ጊዜ ከ5 አመት መብለጥ የለበትም፡፡

➖የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ከሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ ወይም ትምህርት ቤት የሚመረቁበትን ቀን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

➖ለሁለተኛ ዲግሪ የሚያመለክቱ አመልካቾች ኮስት ሼሪንግና ሌሎች የሚከፈሉ ወጪዎችን ከፍለው ዋናው ሰነዳቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

➖የአመልካቾች አላማ መሆን ያለበት መማር ብቻ ነው፡፡ ለሌላ አላማዎች ወይም ቪዛ ብቻ ለማግኘት የሚመጡ አመልካቾችን አንቀበልም፡፡

ጠቅላላ መረጃ

ለጊዜው የሩስያ ቋንቋ ብቻ ነው ለማመልከት ክፍት የሆነው

የተማሪ ቪዛዎች የሚገኙት ኢትዮጵያ በሚገኘው የሩስያ ኢምባሲ (የቆንስላ ቢሮ) በኩል ሲሆን፣ አንድ የተማሪ ቪዛ የሚሰጠው ለ3 ወራት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ይህ የጊዜ ገደብ ካለፈ፣ በሩስያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር ለሚገኘው የስደተኞች ጉዳዮች አስተዳደር ቢሮ የቪዛ ማራዘሚያ ማመልከቻ ማቅረብ ግድ ይልዎታል፡፡ FMS ደጋግመው ከሩስያ መውጣትም ሆነ ወደ ሩስያ መግባት የሚችሉበትን ለአንድ አመት የሚያገለግል ቪዛ ይሰጥዎታል፡፡
ቪዛዎት የአገልግሎት መስጫ ጊዜው ሊያበቃ ሲቃረብ፣ ለተጨማሪ አንድ አመት እንዲራዘምልዎት ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡ የትምህርት ቆይታዎ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በሚኖርዎት ጊዜ ሁሉ፣ በተመሳሳይ መልኩ ቪዛዎትን ማራዘም ግድ ይልዎታል፡፡

1. ማድረግ የሚገባዎች የመጀመሪያው ነገር፣ በሩስያ ከሚገኙ የተቋማችን አጋር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የፈለጉትን ዩኒቨርሲቲና የትምህርት አይነት መምረጥ ነው፡፡ ምርጫውን በዌብሳይታችን፣ በቴሌግራም ቦታችን ወይም ቢሯችን ድረስ በአካል በመምጣት ማከናወን ይችላሉ፡፡

2. የትምህርት አይነቶችን ከመረጡ በኋላ፣ አስፈላጊ የሆኑ የማመልከቻ ሰነዶችን በሙሉ ስካን በማድረግ ይላኩልን፡፡

3. ይህን ተከትሎ፤ ቦሌ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው ቢሯችን በመምጣት ቅድመ ክፍያ እንዲፈጽሙና የማመልከቻ ሂደቱን ለመጀመር የሚያስችልዎትን የስራ ስምምነት ውል እንዲፈጽሙ ጥሪ እናቀርብልዎታለን፡፡

4. ማመልከቻዎትን ወደ ዩኒቨርሲቲው እንልክልዎታለን፤ ከዚያም የሚያገኙትን ነጻ የትምህርት ዕድል መጠን ለመወሰን የሚያስችል የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ ሁኔታዎችን እናመቻችልዎታለን፡፡ የመግቢያ ፈተናው ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅበት ሲሆን፣ በተመቸዎት ጊዜና በድረገጽ አማካይነት የሚከናወን ነው፡፡

5. ዩኒቨርሲቲው ማመልከቻውን መቀበሉን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይልካል፡፡ በዚህ ወቅት የትምህርት ማስረጃዎንና ፓስፖርትዎን የትርጉም ስራ ፈቃድ ባለው ህጋዊ ተቋም አማካይነት ወደ ሩስያኛ ቋንቋ ማስተርጎምና የተተረጎሙት ሰነዶች ትክክለኛ መሆናቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ ኢምባሲ ማረጋገጥ ይጠበቅብዎታል፡፡

6. በተመሳሳይ መልኩም፤ የመጀመሪያውን ሴሚስቴር የትምህርት ክፍያ በትምህርት ቤቱ የባንክ ሒሳብ በኩል መፈጸም ይጠበቅብዎታል፡፡

7. ዩኒቨርሲቲው የግብዣ ሰነዶችን ማዘጋጀት ይጀምራል፤ ሂደቱ በአብዛኛው እስከ 45 ቀናት ይፈጃል፡፡ የግብዣ ሰነዶች ዝግጁ መሆናቸውን ተከትሎ፣ አዲስ አበባ ለሚገኘው የሩስያ ኢምባሲ የተማሪ ቪዛ ማመልከቻ ማስገባትና አጠቃላይ ሂደቱን አጠናቅቀው ትምህርትዎን ለመጀመር ወደ ሩስያ መብረር ትችላላችሁ፡፡

አንድ ተማሪ ሩስያ ውስጥ በግሉ ለመኖር በወር ከ150 እስከ 200 የአሜሪካ ዶላር በቂው ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወር ከ12 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎችን ማግኘት ይቻላል፡፡ ደረጃቸውን የጠበቁ መኝታ ክፍሎችን ደግሞ ከ46 ዶላር ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡

Currently We have active scholarship opportunity to Russia for bachelor and masters level. After submitting your high school transcript, we will arrange an online university entrance exam for you. The exam is free of charge. Depending on the results obtained, you will receive a scholarship for the entire period of study. The exam has over 200 points. If you get
ከ131-150 ውጤት ካመጡ፣ የ10% የትምህርት ክፍያ ቅናሽ
ከ151-170 ውጤት ካመጡ፣ የ25% የትምህርት ክፍያ ቅናሽ
ከ171-180 ውጤት ካመጡ፣ የ40% የትምህርት ክፍያ ቅናሽ
ከ181-190 ውጤት ካመጡ፣ የ60% የትምህርት ክፍያ ቅናሽ
ከ191- 200 ውጤት ካመጡ፣ የ80% የትምህርት ክፍያ ቅናሽ ይደረግልዎታል፡፡

ይህም ማለት፣ በመግቢያ ፈተናው ወይም በቃለመጠይቅ 80 በመቶ ውጤት ካገኙ፣ በሴሚስቴር ለትምህርት የሚከፍሉት ክፍያ እስከ 275 የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ሊል ይችላል፡፡
መደበኛው የትምህርት ክፍያ በአመት 2 ሺህ 800 የአሜሪካ ዶላር መሆኑን፣ እዚህ ላይ ልብ ማለት ያሻል፡፡

በሩስያ እንደሚኖር አለማቀፍ ተማሪ በአገሪቱ ውስጥ ማንኛውንም ተሽከርካሪ መንዳት የሚችሉት አለማቀፍ የመንጃ ፈቃድ ካለዎት ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ በሩስያ አለማቀፍ መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ሃሳብ ካለዎት፣ ከኢትዮጵያ ከመውጣትዎት በፊት ማመልከቻ ማስገባት ይጠበቅብዎታል፡፡ የመንጃ ፈቃዱ ፖላንድ ከገቡ ጊዜ አንስቶ ለ6 ወራት ያህል አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው፡፡ ከ6 ወራት በኋላ ግን፣ ፖላንድ ውስጥ የማሽከርከር ስልጠናዎችን በአግባቡ በመውሰድና ፈተናውን በጥሩ ውጤት በማለፍ የሩስያን ብሔራዊ የመንጃ ፈቃድ ማውጣት ይጠበቅብዎታል፡፡

አለማቀፍ የመንጃ ፈቃድ ለማግኘት በአገር ቤት ያወጡትን የመንጃ ፈቃድ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ የመንገዶችና ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ማቅረብና አለማቀፍ እንዲደረግልዎት ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡ አለማቀፍ የመንጃ ፈቃዱን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በሩስያ ኢምባሲ ማረጋገጫ እንዲሰጠው ማድረግም ግድ ይለዎታል፡፡

አለማቀፍ ተማሪዎች በትርፍ ጊዚያቸው በሚማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ስራ መስራት ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ የዩኒቨርሲቲዎች አለማቀፍ ቢሮዎች ተማሪዎቻቸው የኮንትራት ስራዎችን የመሳሰሉ የስራ ዕድሎችን እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል፡፡ ተማሪዎች መስራት የሚችሉት በፈቃዳቸው ላይ በተጠቀሱት የሙያ መስኮችና ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በብዛት ከሚገኙት ስራዎች መካከል እንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር፣ የምርምርና ጥናት ድጋፍ መስጠትና በሬስቶራንቶች ተቀጥሮ መስራት ይገኙበታል፡፡
በሩስያ አንደስ ተማሪ የትርፍ ሰዓት ስራ በመስራት በወር ከ200 እስከ 300 የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት ይችላል፡፡ ምንጭ፡ በአዲስ አበባ የሩስያ ኢምባሲ ድረገጽ

ይከተሉን!

አድራሻ

1. ቦሌ ከ መድሃኔአለም ሞል ፊት ለፊት፣ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ

+251 115 58 97 94 , +251 116 67 13 76 , +251 116 67 16 93 , +251 942 12 96 11

አድራሻ

2. ለቡ ከጋራ ማርት ፊት ለፊት፣ ፎዚያና ህንጻ 5ኛ ፎቅ

+251 11 470 10 00 , +251 114 70 04 36 , +251 114 70 04 37 , hello@lineaddis.com