ላይን አዲስ ኮንሠልታንሲ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ ለማገዝ በሰኔ ወር 2009 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት፡፡ ላይን አዲስ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ህጋዊ እውቅና አግኝቶ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ሁለት ቢሮዎችን በመክፈት፣ ላለፉት 4 አመታት የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደስተኛ ደንበኞችን ለማፍራት ችሏል፡፡
ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የበለጠ በማዘመንና በማስፋፋት በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው ካሰቡት ግብ እንዲደርሱና ስኬታማ እንዲሆኑ በማገድ ረገድ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
"የደንበኞቻችን ጉዳይ የእኛ ጉዳይ ነው" የሚል መሪ ቃል አንግቦ የሚሰራው ላይን አዲስ የትምህርት አማካሪ ድርጅት ከምንም በላይ ደንበኞቹ ለሆኑ ተማሪዎች ስኬት ትኩረት የሚሰጥና ከደንበኞቹ የሚሰጡትን አስተያየት፣ ትችትና ምክሮች በአክብሮት ተቀብሎ በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ የማያመነታ ራሱን ለመለወጥና ለማሳደግ ወደኋላ የማይል ድርጅት ነው፡፡
1. መሄድ የምትፈልጉበትን አገር እና መማር የምትፈልጉትን ኮርስ ከድረ-ገጻችን ላይ ምረጡ፡፡ ለመምረጥ እዚህ ይጫኑ በአገር፣ በምትፈልጉት ኮርስ እና በዲግሪ ደረጃ ለይታችሁ መምረጥ ትችላላችሁ፡፡
2. ሁሉንም ሰነዶች ስካን አድርጋችሁ ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች አንዱን መርጣችሁ መላክ ትችላላችሁ፡፡
ኢ-ሜይል:
hello@lineaddis.com
ቴሌግራም:
@lineaddis2
ዌብሳይት:
ለመጀመር እዚህ ይጫኑ
ኦሪጅናል ሰነዶችን ይዘው መስሪያ ቤታችን ይምጡ እኛ ስካን እናደርጋለን፡፡
3️. መስሪያ ቤታችን በአካል በመገኘት ቅድመ ክፍያ እና ህጋዊ ውል መፈጸም፡፡
- ከአዲስ አበባ ውጭ ለምትኖሩ አመልካቾች ውሉን ፈርመን በኦንላይን መላክ እንችላለን፤ ወይም ተወካይ መላክ ትችላላችሁ፡፡
4️. የተቀባይነትን ደብዳቤ ከዩኒቨርሲቲዎች በምትጠብቁበት ጊዜ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በቪዲዮ ቃለመጠይቅ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡
5️. የተቀባይነትን ደብዳቤ ከዩኒቨርሲቲዎች በምትጠብቁበት ጊዜ የማመልከቻ ክፍያ ከት/ቤት ክፍያ ጋር መክፈል ሊጠበቅባቸው ይችላል፤ ወይም በቀጥታ ወደ ትምህርት ቤቱ አካውንት ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ የተቀባይነት ደብዳቤው ላይ ያለው ነገር በዝርዝር ይጠቅማል፡፡
6️. አስፈላጊውን ክፍያ ለዩኒቨርሲቲው ከፈጸማችሁ በኋላ ዋናው የተቀባይነት ደብዳቤ ከተለያዩ ሰነዶች ጋር አብሮ ይደርሳችኋል፡፡ ለምሳሌ ሄዳችሁ ስለምታርፉበት ቦታ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ ለቪዛ ማመልከት እንድትችሉ የሚረዳ ደብዳቤ፡፡
7️. በዚህ ወቅት ለቪዛ የሚያስፈልጉ ሠነዶችን ማዘጋጀት ይጠበቅባችኋል፡፡
- የስፖንሰር ሠነዶች - ስንፖንሰር የሚያደርጋቸው ሰው የባንክ ስቴትመንት፣ የገቢ ምንጭ የሚያሳይ ደብዳቤ፣ የስፖንሰሩ መታወቂያ እንዲሁም የስፖንሰሩ ቃለመሃላ፡፡ ይህ የተጠቀሰው ሂደት በምታመለክቱበት ኤምባሲ የሚለይ ሲሆን፣ የስፖንሰር ሠነዶችን ላትጠየቁም ትችላላችሁ፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉልን፡፡
- የጤና ሰርተፊኬቶች - አንዳንድ አገሮች የጤና ሰርተፊኬቶችን ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉልን፡፡
- ኢምባሲ መግቢያ ፎርም
- የተቀባይነት ደብዳቤ
- ህጋዊ የትምህርት ሰነዶች
- የጉዞ /የጤና/ ኢንሹራንስ
እያንዳንዱ ኤምባሲ የተለያዩ ሠነድ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉልን፡፡
8️. ኤምባሲ ለቃለ-መጠይቅ ከመግባታቸው በፊት - የምንሰጣቸው ስልጠና ይኖራል፡፡ እንዲሁም ማዘጋጀት ስለሚኖርባቸው ሠነዶች ዝርዝር የምንነግራቸው ይሆናል፡፡
9️. በትክክለኛው ኤምባሲ/ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ማመልከታችሁን አረጋግጡ፡፡
10. ቪዛ ሲመታላቸው፣ ከመሄዳቸው በፊት ማወቅ ስላለባቸው ነገሮች፣ ስለምታርፉበት ቦታ፣ ከአየር ማረፊያ ወዴት እንደምትሄዱ ወዘተ ያለውን ሂደት በዝርዝር የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡
ይበልጥ ለመረዳት ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ
ደንበኞቻችን ስለ እኛ ምን እንዳሉ ለማንበብ ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ
ዮቲዩብ ላይ ደንበኞቻችን ስለ እኛ ምን እንዳሉ ለማየት ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ
ህጋዊነታችንን የሚያሳዩ ከአጋር ዩኒቨርሲቲዎቻችን የተላኩ ደብዳቤዎችን ማየት ትችላላችሁ፡፡
መስሪያ ቤታችን በአካል መጥተው ንግድ ፈቃድና ህጋዊ ሠነዶቻችንን ማየት ትችላላችሁ፡፡
ህጋዊ ውልን ይፈራረሙ፤ በንግግር መፈታት የማይችሉ አለመግባባቶች ከተፈጠሩ በህግ ሊጠይቁን የሚችሉት ሠነድ ነው፡፡
ሌሎች ማስረጃዎችን የምትፈልጉ ከሆነ፣ ለመደወል አያመንቱ፡፡ እኛን ለማግኘት ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ
1. ሰዓት አክባሪነት
2. ዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያዎች
3. 95% የቪዛ ስኬት መጠን
4. የ 5 አመት የስራ ልምድ
5. ዕውቅና
እኛን ለምን ይመርጣሉ (ቪዲዮ)