አገልግሎቶቻችን

Admission to Universities
በዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት ማስገኘት

በዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት ማስገኘት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች አስፈላጊ የቅድመ ምዝገባ ገለጻና የማማከር አገልግሎት ከመስጠት አንስቶ በውጭ አገራት በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ማመልከቻ ከማስገባት እስከ ጉዞና የትምህርት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች አለማቀፍ ተሞክሮዎችን ባገናዘበና በአግባቡ በተዋቀረ አሰራር የሚከናወኑ ሲሆን፣ በዘርፉ ለረጅም አመታት በሰሩ ባለሙያዎቻችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ረጅሙን ሂደት የሚያሳጥሩና በቀላሉ ለስኬት የሚያደርሱ ናቸው፡፡

በዘርፉ በባለሙያዎቻችን ያሰራናቸውን ጥናቶች መሰረት በማደረግ ደንበኞች ትክክለኛውን ትምህርትና የትምህርት ተቋም እንዲመርጡ ድጋፍ ከማድረጋችን በተጨማሪም፣ የደንበኞቻችንን ፍላጎትና የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ ማመልከቻዎቻቸው ተቀባይነት እንዲያገኙ በተለያዩ የአለማችን አገራት ከሚገኙ ስመጥር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስምምነት መፈጸማችንንም ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Visa Application
የቪዛ ማመልከቻዎች

ከፍተኛውን የቪዛ ስኬት መጠን ለማሳካት ለቪዛ ማመልከቻዎ ግልጽ የሆነ ስልጠና እና መመሪያን እንሰጣለን፡፡ በተጨማሪም ለቪዛ ማመልከቻዎ የሚያስፈልጉዎትን እያዳንዱ ሰነድ እንዲያዘጋጁ ለሚመለከታቸው ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽህፈት ቤት ጉብኝትዎን እንዲያዘጋጁ እና ለቃለመጠይቅ እንዲዘጋጁ እናግዝዎታለን፡፡ ባለፉት 5 አመታት ውስጥ የ95 በመቶ የቪዛ ስኬት መጠንን አስመዝግበናል፡፡

Scholarship Applications
የስኮላርሺፕ ማመልከቻዎች

በተለያዩ የአለም አገራት በሚገኙ ስመጥር ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች የተዘጋጁ የተለያዩ የስኮላርሺፕ ዕድሎች አሉ፡፡ እንዳልመታደል ሆኖ ግን፣ በማመልከቻዎች ላይ በቂ መረጃ ባለመኖሩ ብዙ ተማሪዎች በእነዚህ እድሎች ተጠቃሚ መሆን አይችሉም፡፡

የመስኩ ባለሙያዎችን እንደነዚህ ያሉትን ዕድሎች እንደሚመርጡበት ከአጋር ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ቅናሾችን እንዲያገኙ እና በሚያመለክቱበት ጊዜ እንዲመሩዎት አድርገናል፡፡ በሰነድና በወረቀት ስራዎች ላይም ድጋፍና እገዛቸው አይለይዎትም፡፡

Online Education
የኦንላይን ትምህርት

በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ብዙ ሰዎች የሙሉ ጊዜ ጥናት ፕሮግራም ለመጀመር እንዳይችሉ ከሚያደርጓቸው አስገዳጅ ምክንያቶች አንዱ ከስራ ተርፎ ለትምህርት የሚውል በቂ ጊዜ አለመኖር ነው፡፡

ከስራ ገበታቸው እረፍት ወስደው የሙሉ ጊዜ ትምህርትን ተከታትሎ መጨረስ አዳጋች ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ ሰራተኞች ደግሞ፣ ብዙውን ጊዜ በስራ ምክንያት ከሚኖሩበት ከተማ ለተራዘመ ጊዜ ለመውጣት ስለሚገደዱ፣ የሙሉ ጊዜ ትምህርት በአንድ ቦታ ላይ ጀምረው ለመጨረስ አይችሉም፡፡ መደበኛ ስራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ፣ ጎን ለጎን ትምህርታቸውን ለመከታተልና በእውቀትና በሙያቸው ወደተሻለ እድገት ለመሸጋገር ለሚፈልጉ፣ የኦንላይን ትምህርት/ የድረገጽ ትምህርት ፕሮግራም ሁነኛ አማራጭ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡

ላይን አዲስ መሰል ፍላጎት ላላቸው ዜጎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ወይም ከቤታቸው ሳይርቁ የአጭር ጊዜ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የድህረ ምረቃ ዲግሪ እና የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው በአግባቡ መማርና ማጠናቀቅ የሚችሉበትን ዕድል አመቻችቷል፡፡ እባክዎ ጎራ ብለው ያማክሩን!

Exam Assistance
የፈተና እገዛ

ከፍተኛ ውድድርና ፉክክር ባለበት የትምህርት ተቋም ውስጥ በተማሪነት ለማመልከት የሚያስቡ ሰዎች ትኩረት ሊሰጡት ከሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች አንዱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት መመዘኛ ፈተና አንዱ ነው፡፡

የቋንቋ ብቃት መመዘኛ ፈተናዎችን በጥሩ ውጤት ማለፍ፣ በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ውድድሮች ውስጥ ጎልተው የመውጣትና የመመረጥ ዕድልዎትን ከፍ በማድረግ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፡፡ እርስዎም መሰል ዕቅድ ካለዎት፣ ላይን አዲስን ያማክሩ፡፡ ለእርስዎ ተስማሚ የሆነውን ፈተና እንዲመርጡ እናግዝዎታለን፤ ለፈተናው የሚያግዙ መረጃዎችንና ቁሳቁሶችን በበቂ መጠን እናቀርብልዎታለን፤ ተገቢውን ክፍያ በመክፈል ከማስመዝገብ ባለፈም በአመቺ ጊዜ ፈተናዎትን የሚወስዱበትን ሁኔታ አመቻችተን በቀላሉ ተፈትነው ውጤታማ የሚሆኑበትን ድጋፍ እንሰጥዎታለን፡፡

Others
ሌሎች ጉዳዮች

በትምህርት ማማከር አገልግሎት ለአመታት መስራታችን የዘርፉን ዋና ዋና ችግሮች፣ ዕድሎች፣ ፈተናዎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በቅጡ ለመገንዘብ አስችሎናል፡፡ ተማሪዎች ከማመልከት አንስቶ እስከ ትምህርት ገበታ ጥናት የሚያጋጥሟቸውን ተደጋጋሚ ፈተናዎች እንዲሁም የሚያስፈልጓቸውን ተገቢ የድጋፍ አገልግሎቶች በሚገባና ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን፤ ለተማሪዎች ተገቢውን አገልግሎትና መፍትሄ በአግባቡ መስጠትና ለስኬት እንዲበቁ ማድረጉንም እናውቅበታለን፡፡

ለደንበኞቻችን ከምንሰጣቸው ዘርፈ ብዙ የድጋፍና እገዛ አገልግሎቶች መካከልም የፋይናንስ መፍትሄዎችን ማፈላለግ፣ የጉዞ ዝግጅት ድጋፍ ማድረግ፣ ለትምህርት በሚሄዱባቸው አገራት የትርፍ ሰዓት የስራ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ የማረፊያ ቦታዎችን ማዘጋጀት፣ ከአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ወደመዳረሻቸው ደህንነታች በተጠበቀ መልኩ የሚወስዳቸው ሰው ማመቻቸት፣ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ እገዛ መስጠትና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ 

በብዛት የሚጠየቁ ጥያቄዎች

1. መሄድ የምትፈልጉበትን አገር እና መማር የምትፈልጉትን ኮርስ ከድረ-ገጻችን ላይ ምረጡ፡፡ ለመምረጥ እዚህ ይጫኑ በአገር፣ በምትፈልጉት ኮርስ እና በዲግሪ ደረጃ ለይታችሁ መምረጥ ትችላላችሁ፡፡

2. ሁሉንም ሰነዶች ስካን አድርጋችሁ ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች አንዱን መርጣችሁ መላክ ትችላላችሁ፡፡
 ኢ-ሜይል: hello@lineaddis.com
 ቴሌግራም: @lineaddis2
 ዌብሳይት: ለመጀመር እዚህ ይጫኑ
 ኦሪጅናል ሰነዶችን ይዘው መስሪያ ቤታችን ይምጡ እኛ ስካን እናደርጋለን፡፡

3️. መስሪያ ቤታችን በአካል በመገኘት ቅድመ ክፍያ እና ህጋዊ ውል መፈጸም፡፡ - ከአዲስ አበባ ውጭ ለምትኖሩ አመልካቾች ውሉን ፈርመን በኦንላይን መላክ እንችላለን፤ ወይም ተወካይ መላክ ትችላላችሁ፡፡

4️. የተቀባይነትን ደብዳቤ ከዩኒቨርሲቲዎች በምትጠብቁበት ጊዜ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በቪዲዮ ቃለመጠይቅ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

5️. የተቀባይነትን ደብዳቤ ከዩኒቨርሲቲዎች በምትጠብቁበት ጊዜ የማመልከቻ ክፍያ ከት/ቤት ክፍያ ጋር መክፈል ሊጠበቅባቸው ይችላል፤ ወይም በቀጥታ ወደ ትምህርት ቤቱ አካውንት ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ የተቀባይነት ደብዳቤው ላይ ያለው ነገር በዝርዝር ይጠቅማል፡፡

6️. አስፈላጊውን ክፍያ ለዩኒቨርሲቲው ከፈጸማችሁ በኋላ ዋናው የተቀባይነት ደብዳቤ ከተለያዩ ሰነዶች ጋር አብሮ ይደርሳችኋል፡፡ ለምሳሌ ሄዳችሁ ስለምታርፉበት ቦታ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ ለቪዛ ማመልከት እንድትችሉ የሚረዳ ደብዳቤ፡፡

7️. በዚህ ወቅት ለቪዛ የሚያስፈልጉ ሠነዶችን ማዘጋጀት ይጠበቅባችኋል፡፡
 - የስፖንሰር ሠነዶች - ስንፖንሰር የሚያደርጋቸው ሰው የባንክ ስቴትመንት፣ የገቢ ምንጭ የሚያሳይ ደብዳቤ፣ የስፖንሰሩ መታወቂያ እንዲሁም የስፖንሰሩ ቃለመሃላ፡፡ ይህ የተጠቀሰው ሂደት በምታመለክቱበት ኤምባሲ የሚለይ ሲሆን፣ የስፖንሰር ሠነዶችን ላትጠየቁም ትችላላችሁ፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉልን፡፡
 - የጤና ሰርተፊኬቶች - አንዳንድ አገሮች የጤና ሰርተፊኬቶችን ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉልን፡፡
 - ኢምባሲ መግቢያ ፎርም
 - የተቀባይነት ደብዳቤ
 - ህጋዊ የትምህርት ሰነዶች
 - የጉዞ /የጤና/ ኢንሹራንስ እያንዳንዱ ኤምባሲ የተለያዩ ሠነድ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይደውሉልን፡፡

8️. ኤምባሲ ለቃለ-መጠይቅ ከመግባታቸው በፊት - የምንሰጣቸው ስልጠና ይኖራል፡፡ እንዲሁም ማዘጋጀት ስለሚኖርባቸው ሠነዶች ዝርዝር የምንነግራቸው ይሆናል፡፡

9️. በትክክለኛው ኤምባሲ/ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ማመልከታችሁን አረጋግጡ፡፡

10. ቪዛ ሲመታላቸው፣ ከመሄዳቸው በፊት ማወቅ ስላለባቸው ነገሮች፣ ስለምታርፉበት ቦታ፣ ከአየር ማረፊያ ወዴት እንደምትሄዱ ወዘተ ያለውን ሂደት በዝርዝር የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡

ይበልጥ ለመረዳት ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ

ደንበኞቻችን ስለ እኛ ምን እንዳሉ ለማንበብ ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ
ዮቲዩብ ላይ ደንበኞቻችን ስለ እኛ ምን እንዳሉ ለማየት ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ

ህጋዊነታችንን የሚያሳዩ ከአጋር ዩኒቨርሲቲዎቻችን የተላኩ ደብዳቤዎችን ማየት ትችላላችሁ፡፡

መስሪያ ቤታችን በአካል መጥተው ንግድ ፈቃድና ህጋዊ ሠነዶቻችንን ማየት ትችላላችሁ፡፡

ህጋዊ ውልን ይፈራረሙ፤ በንግግር መፈታት የማይችሉ አለመግባባቶች ከተፈጠሩ በህግ ሊጠይቁን የሚችሉት ሠነድ ነው፡፡

ሌሎች ማስረጃዎችን የምትፈልጉ ከሆነ፣ ለመደወል አያመንቱ፡፡ እኛን ለማግኘት ፡ እዚህ ክሊክ ያርጉ

1. ሰዓት አክባሪነት

2. ዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያዎች

3. 95% የቪዛ ስኬት መጠን

4. የ 5 አመት የስራ ልምድ

5. ዕውቅና

እኛን ለምን ይመርጣሉ (ቪዲዮ)

ይከተሉን!

አድራሻ

1. ቦሌ ከ መድሃኔአለም ሞል ፊት ለፊት፣ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፎቅ

+251 115 58 97 94 , +251 116 67 13 76 , +251 116 67 16 93 , +251 942 12 96 11

አድራሻ

2. ለቡ ከጋራ ማርት ፊት ለፊት፣ ፎዚያና ህንጻ 5ኛ ፎቅ

+251 11 470 10 00 , +251 114 70 04 36 , +251 114 70 04 37 , hello@lineaddis.com